ግራዝማች ናደው ወረታ – የሰሜን ተራሮች ፓርክ መስራች:: Girazmach Nadew Woreta

ኢትዮጵያ የብዙ ጀግኖች ማፍሪያ የታሪክ ማህደሯ በጀግኖች ታሪክ የሞላ አሁንም በጀግኖች የታጠረች አገር ናት::ዛሬ ከጀግኖቻችን አንዱ ስለሆኑት ግራዝማች ናደው ወረታ የጀግንነት ታሪክበአጭሩ ለመዘከር እንሞክራለን:: ግራዝማች ናደው ወረታ ቢትዮጵያ የሰሜን ተራሮች በጎንደር ክፍለሃገር በልዩ ስፍራ አምባራስ በሚባል አከባቢ ተወለዱ::ለአቅመ አዳም እስኪደርሱ ድረስ በአከባቢያቸው ጠንካራ ስራዎችን woretaሲሰሩ የነበሩት ግራዝማች ታላላቅ ስራዎችን ሰርተው አልፈዋል:: የአከባቢው አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት ግራዝማች ናደው በአጼ ሃይልስላሴ ዘመን የፓርላማ አባል በመሆን ያገለገሉ ሲሆን ታላቅ ፖለቲከኛ ሕግ አውጪ እና አማካሪ ጠበቃ በመሆን ታላቅ ስራዎችን ለሕዝባቸው አበርክተዋል::ከዚህ ጋር በተያያዘ የሰሜን ተራሮችን ፓርክ በመመስረት ረገድ ከፍተኛውን እና ግንባር ቀደም ሚና ተጫውተዋል::የአከባቢውን ነዋሪዎች በማስተማር በማስተባበር በማቀናጀት ከመጀመሪያ ጀምሮ የደን ጭፍጨፋን ስለመከላከል የደን ጥበቃን ወዘተረፈ በማስተማር የፓርኩ ዋና ተንከባካቢ በመሆን ድርሻቸውን አበርክተዋል:: በተፈጥሮ መልካምነትን ያደላቸው ግራዝማች ናደው እጅግ ሩህሩህ ያላቸውን የሚያካፍሉ ለሰው አዛኝ ረዳት እና ታታሪ ነበሩ:: በሃገራችን አንድ የተለመደ ነገር አለ ለህዝብ እና ለሃገር አስታውጾ ያበረከቱ እና የጥሩ ጀግኖች አስታዋሽ ማጣታቸውን እና መልካም ዋጋቸውን አለማግኘታቸው የሚያሳዝን ጉዳይ ነው::ግራዝማች ቢያልፉም ስራቸው ህያው ሆኖ ይታወሳል በተግባርም እየታይ ሌላዉንም እያበረታታ ነው:;የሰሜን ተራሮች ፓርክን ለቱሪዝም መስሕብነት በማብቃት በዛሬው ጊዜ ላይ በሺዎች የሚቆተሩ ቱሪስቶች ፓርኩን በመጎብኘት ለሃገሪቱ የውጪ ምንዛሬ ግኝት የግራዝማች ፈር ቀዳጅነት የማይረሳ ታላቅ ስራ ነው::እንዲሁም በፓርኩ ውስጥ በቱሪዝም መስክ በርካታ የስራ እድሎችን ለዜጎች በመክፈት ታላቅ ስራ ሰርተው አልፈዋል::ይህ ስራቸው ከተወሰኑ ሰዎች እና ከቤተሰባቸው ታሪኩ ሊነገር አለመቻሉ እስካሁን በሰፊው ሳይነሳ ቆይቷል:: ግራዝማች በሕይወት ባርኖሩም ለቤተሰባቸው ትተው ባለፉት ጥንካሬ እና በምክር የተገነባ የሞራል ታላቅነት እሳቸው ሌናት ሃገራቸው ያደረጉት አስታውጾ እና ለሕዝባቸው በሰሩት መልካም ስራ ሲያስታውሳቸው መጭው ትውልድ እንዲበረታታ እንዲንቀሳቀስ እና የተረሱ ጀግኖች እንዲታወሱ የጋራ የሆነ የዜግነት ሃላፊነት አለብን:: ስልዚህ እንደ EWCA እና እንደ ፓርክ ጽ/ቤቶች ያሉ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት እና ሌሎች ለጉዳዩ አትኩሮት በመስጠት ለፓርኩ እድገት የሚደረጉ ስራዎችን በማስፋት እና በማዳበር ሰፊ ስራዎች እንዲሰሩ አገራዊ ግዴታችንን በአንድነት ልንወጣ ይገባል:: በመጨረሻ ለማለት የምፈልገው ለግራዝማች ናደው ወረታ እና ለቤተሰባቸው ያለኝን ጥልቅ አድናቆት እየገለጽኩ ለሰሜን ተራሮች ፓርክ መመስረት ላበረከቱት አስታውጾ እያደነኩ ግራዝማች ያልተነገሩ ብዙ ታሪኮች ያሏቸው ሲሆኑ ወደፊት በሰፊው የምመለስበት ሲሆን ለዛሬው በዚህ ይብቃን:: ፈጣሪ ውለታቸውን ይክፍላቸው ነብሳቸውን ይማር ::ከአክብሮት ጋር::

 

Girazmach Nadew Woreta
Ethiopia had and still has many heroes in her ancient history. Today I want to post just short life story about one of the heroes, Girazmach/title name/ Nadew Woreta. Girazmach was born in the Simen Mountains of Ethiopia particularly in a village called Ambaras, Ever since he started understanding his surrounding he did many great things, he was working as a local administrator, he was also elected as a member of the parliament during Emperor Haile Silassie, he was acting like a politician, law giver and consultant etc of his own people. In this case what I would like to write is about what he did for the Simen Mountains National Park, He really did a great job for the establishment of the park by educating the local people as they were very persistent from the beginning, protecting poaching, deforestation and I can confidently say that he was one of the pioneers of the park.
Being naturally gifted person Girazmach was kind-hearted, sociable who wants to share everything that he had with others. One thing which makes me sad is it is a pity people like him do not get their price at the end,Girazmach has passed away but his nice jobs exist up until now, one of his visible jobs is tourism is now growing every year in the Simen Mountains which is opening a good job opportunity for thousands of jobless people but just very few people remember him and his family.
Even though Girazmach is not alive giving a reward to his family is so advisable and this builds their morality because it is absolutely important to remember those who did nice job for their people and motherland so that the future generation will be encouraged and motivated. Therefore, concerned bodies like EWCA, Park office and others should pay attention since we are thinking about sustainable development.
Last but not least I would like to express my enormous compliment to him and his beloved family for their great contribution of the foundation of the park.
Girazmach has more untold stories I just posted what I know but will be back with additional ones in the future.
May God pay him his price and put his soul in heaven.
With great respect!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *